የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ አገኘ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመገናኛ ብዙሃን ተቋም የሆነው የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ፣ የህዝብ ብሮድካስት የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይፋዊ ፈቃድ ዛሬ አግኝቷል። ይህ ፈቃድ የሚዲያ ተቋሙ የክልሉን ማህበረሰብ በተሟላ መረጃ ለማገልገል የጀመረውን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ታሪካዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። በዛሬው ዕለት በባለስልጣኑ ጽ/ቤት በተካሄደው የፈቃድ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ…

