ማንኛውም ሀገራዊ ሽግግር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው፣ ሂደቱን የሚመሩ አካላት የኃላፊነት ወሰንን በተመለከተ በኅብረተሰቡ ዘንድ የተሟላ ግንዛቤ እና ግልፅነት ሲፈጠር ብቻ ነው።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የነገዋን የበለፀገች ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ነው። የዚህን ታላቅ መድረክ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ታዲያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የኃላፊነት ወሰን እና ሚና በማብራራት አንዳንድ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ማረም ይገባል። በተወሰኑ አካላት ዘንድ የሚስተዋለው ዋነኛው የተሳሳተ ግንዛቤ፣ ኮሚሽኑን እንደ አንድ የመጨረሻ “የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ” ወይም “ሕግ አውጪ” አካል አድርጎ ማየት…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። ‎በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ቁልፍ ስምምነቶች ልውውጥን በጋራ የመራን ሲሆን፤ የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት፣ እና የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ ይገኙበታል።

Read More