በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የወሰዱ ዜጎች ቁጥር ከ41 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ መረጃ ያመለክታል።
ተቋሙ በ2018 ዓ.ም ዲጂታል መታወቂያውን ለ70 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ ይገኛል።
በዓመቱ 160 ተቋማትን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት 9 ወራት 132 ድርጅቶችን ከሥርዓቱ ጋር ማገናኘት ተችሏል።
በሌላ በኩል፣ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት ለማበልጸግ እየተተገበረ ባለው የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና፣ እስከአሁን 4 ሚሊዮን 506 ሺህ 27 ዜጎች ተመዝግበዋል።
በ2018 ዓ.ም የሰልጣኞች ቁጥርን 4 ሚሊዮን 484 ሺህ ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፣ እስከአሁን 3 ሚሊዮን 376 ሺህ 17 ዜጎች ስልጠናውን በስኬት መጠናቀቃቸውን ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ይህም ለተጀመረው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።



