የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የመደመር መንግስትና የብልጽግና ፓርቲ የአየር ሚዛን መጠበቂያ ትልቁ ፕሮጀክት ነው- ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻር መርሐ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ገሊት በይፋ ተጀምሯል።

‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ መርሐግብር ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የመደመር መንግስትና የብልጽግና ፓርቲ የአየር ሚዛን መጠበቂያ ትልቁ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

‎የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የዓለም አየር ሚዛን ከመጠበቅ ባሻገር ጥምር ግብርና እና የአትክልት ልማት ስራዎች ያካተተ በመሆኑ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል።

‎በክልል ደረጃ 25 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር የሚተከሉ መሆናቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ በአገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር ይተከላሉ ብለዋል።

‎አረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር ተተክሎ የሚተው ሳይሆን በዘላቂነት የሚቀጥል ተግባር በመሆኑ በተጀምረው መንገድ አጠናክሮ ማስቀጠል እና የተተከሉትን ችግኞች የመንከባከብ ስራ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

‎መላው የክልሉ ማህበረሰብ ክፍል ይህ አገራዊ ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን በክልሉ የተዘጋጁ የተከላ ጉድጓዶች እስኪጠናቀቁ የተከላ ስራው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

‎የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን መንገሻ በበኩላቸው አረንጓዴ አሻራ ለዞኑ ማህበረሰብ የስነ-ምህዳር ጥበቃ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

‎በዞኑ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማት ስራም በስፋት የሚከናወንበት በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

‎የደቡብ ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ ኪያስካ በበኩላቸው ሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ ለአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ተግባሩ በወረዳው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x