ማንኛውም ሀገራዊ ሽግግር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው፣ ሂደቱን የሚመሩ አካላት የኃላፊነት ወሰንን በተመለከተ በኅብረተሰቡ ዘንድ የተሟላ ግንዛቤ እና ግልፅነት ሲፈጠር ብቻ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የነገዋን የበለፀገች ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ…
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የነገዋን የበለፀገች ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ነው። የዚህን ታላቅ መድረክ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ታዲያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የኃላፊነት ወሰን እና ሚና በማብራራት አንዳንድ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ማረም ይገባል። በተወሰኑ አካላት ዘንድ የሚስተዋለው ዋነኛው የተሳሳተ ግንዛቤ፣ ኮሚሽኑን እንደ አንድ የመጨረሻ “የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ” ወይም “ሕግ አውጪ” አካል አድርጎ ማየት…
“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻር መርሐ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ገሊት በይፋ ተጀምሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ መርሐግብር ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የመደመር መንግስትና የብልጽግና ፓርቲ የአየር ሚዛን መጠበቂያ ትልቁ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የዓለም አየር…
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል “ከልመና ወደ ብልፅግና” የመሻገርና አገራዊ ክብርን የማስጠበቅ ግብ በመሰነቅ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ቃል በሐዋሳ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአደጋ…
በክልላችን የሚገኙ 48 ወረዳዎችን ታላሚ ያደረገውና ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መድኃኒት የሚያገኙበት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቢሮ ሀላፊ ተወካይ አቶ ኃይሌ ዘውዴ ዘመቻውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ “ህብረተሰቡን ለጤናና ለማህበራዊ ጉዳት የሚዳርጉ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎችን ለማጥፋት የሚሰጠው መድኃኒት ውጤታማ እንዲሆን የሁሉንም አካላት ቅንጅታዊ ስራ ይጠይቃል” ብለዋል።…
በምርጫ ወቅት የፖሊስ ሚናና ስነምግባር በሚል ርዕሰ ጉዳይ በካፋ ዞን ለሚገኙ የፖሊስ አባላት በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ። በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር በላይነህ በቀለ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተሳተፊ የሚሆኑ የጸጥታ አካላት ሚናቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መረዳትና ማወቅ ይገባቸዋል ብለዋል። ይህም ምርጫው በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅና የፖሊስ አባላት ስነምግባርን…
ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ቁልፍ ስምምነቶች ልውውጥን በጋራ የመራን ሲሆን፤ የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት፣ እና የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ ይገኙበታል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በመገኘት ለ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂደዋል። በዞኑ ጀሙ ከተማ በተካሄደው የይምረጡኝ ቅስቀሳ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ባለፉት ዓመታት በሰጣችሁን ይሁንታ መሰረት ላከናወንነው ተግባራት ከጎናችን መሆናችሁን በይፋ ስለገለጻችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ የነበረውን ኋላ ቀርነትና…
በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ካስሜሮ እና ቤንጃሚን ሼሽኮ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ማቲያስ የንሰን የብሬንትፎርድን አንድ ግብ አስገኝቷል። ከጨዋታው ሦስት ነጥብ ያገኘው ዩናይትድ በ61 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የወሰዱ ዜጎች ቁጥር ከ41 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ መረጃ ያመለክታል። ተቋሙ በ2018 ዓ.ም ዲጂታል መታወቂያውን ለ70 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ ይገኛል። በዓመቱ 160 ተቋማትን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት 9 ወራት 132 ድርጅቶችን ከሥርዓቱ ጋር ማገናኘት ተችሏል። በሌላ በኩል፣ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት ለማበልጸግ እየተተገበረ ባለው…