ማንኛውም ሀገራዊ ሽግግር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው፣ ሂደቱን የሚመሩ አካላት የኃላፊነት ወሰንን በተመለከተ በኅብረተሰቡ ዘንድ የተሟላ ግንዛቤ እና ግልፅነት ሲፈጠር ብቻ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የነገዋን የበለፀገች ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለመ ነው። የዚህን ታላቅ መድረክ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ታዲያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የኃላፊነት ወሰን እና ሚና በማብራራት አንዳንድ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ማረም ይገባል። በተወሰኑ አካላት ዘንድ የሚስተዋለው ዋነኛው የተሳሳተ ግንዛቤ፣ ኮሚሽኑን እንደ አንድ የመጨረሻ “የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ” ወይም “ሕግ አውጪ” አካል አድርጎ ማየት…

