ለፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን እየተሰሩ የሚገኙ የታርጫ-ጪዳ አስፓልት መንገድ፣ የወልድሃኔ ዱርጊ-ዱራሜ መንገድና የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለህዝቡ ጥቅም የሚውሉ መሆን እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

‎በሚቀጥሉት ወራት በሁሉም ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ በዛብህ በበኩላቸው የሚነሱ ማነቆዎች በተገቢው በመፍታት፤ በሚቀጥሉት 2 እና 3 ወራት በተለይ የታርጫ-ጪዳ መንገድ ካለበት ደረጃ የሚታይ ለውጥ እንዲያስመዘግብ አሳስበዋል።

የወልድሃኔ_ዱርጊ_ዱራሜ መንገድ ግንባታ ዙሪያ ያሉ መነቆዎች የተነሱ ሲሆን በዳውሮ በኩል ያለው ያነሰ አፈፃፀም በፍጥነት እንዲታረም አስገንዝበዋል።

‎በክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ካሉት ማዕከላት የታርጫው የተሻለ አፈፃፀም ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የመቆራረጥ ጉዳዮች ቢቀረፉ ከተያዘለት ሰኔ 2019 የጊዜ ገደብ ቀድሞ የመጠናቀቅ ዕድል አለው ተብሏል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x