የመደመር መንግስት ለህዝብ ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠት የክልሉን ሁለንተናዊ ብልፅግና ያረጋግጣል- ርዕሰ መስተዳድር ፍቅሬ አማን

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከዳውሮ ህዝብ ጋር በታርጫ ከተማ እየመከሩ ነው።

‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመደመር መንግስት ባለፉት አመታት የክልሉን ህዝቦች የልማትና ዴሞክራሲ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

‎በተጨማሪም የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተደረገ የሚገኘው ጥረት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፤ ያለውን ፀጋ ወደ ተጨባጭ ለውጥ ለመቀየር የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

‎የክልሉ መንግስት ከዞኑ ህዝብ ጎን እንደሚቆምና አመራሩ በአገልጋይነት መንፈስ ተግባሩን እንደሚያከናውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

‎የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትዕዛዙ ባዩ በበኩላቸው ህዝቦች ለዘመናት ምላሽ ተነፍገው የቆዩበት ስርዓት ተወግዶ በለውጡ መንግስት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

‎ለዚህም ማሳያ በዞኑ የመንገድ መሠረተ ልማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መስፋፋትን እንደ አብነት ጠቅሰዋል።

‎የክልሉ መንግስት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሠረት በዞኑ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ በቀጣይ የልማት ስራዎችን ለማሳለጥ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x