በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት የ2019 በጀት ዓመት የየዘርፎች ስትራቴጂያዊ ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክርና የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ህዝቡ በምርጫ ወቅት የሰጠንን ታላቅ አደራ እና እምነት በልበ ሙሉነት ወደ ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም የአመራሩ ተቀዳሚ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።
“ጠንካራ ፓርቲ ፤ ለጠንካራ መንግሥት” መርህ በመከተል በፓርቲው የተነደፉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ኢኒሼቲቮችን በአግባቡ በመምራትና በማስተባበር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
የአመራሩንና የአባሉን አቅም የሚያሳድጉ መደበኛ ሥልጠናዎችን በመስጠት የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት፣ እንዲሁም የፓርቲውን የመፈፀምና ማስፈፀም አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የወጣቶችንና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ዘመናዊና ዲጂታል አሠራሮችን በመጠቀም የፓርቲውን ግቦችን ማሳካት ጊዜው ይጠይቃል ብለዋል።
የፓርቲውን ተቋማዊ አደረጃጀቶች በማጠናከር የትርክት የበላይነትንና ቅቡልነትን ማረጋገጥ፣ የፓርቲውን እሳቤዎች፣ ዓላማዎችና አገራዊ ስኬቶችን በሰፊው ማስረጽ ያስፈልልጋል ነው ያሉት።
ወንድማማችነት/እህትማማችነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ፣ የተቀመጡትን ስትራቴጂያዊ ግቦች ወደ ተግባር ለመለወጥና የተጣለባቸውን የህዝብ አደራ በአግባቡ ለመወጣት አመራሩና አባሉ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።
የፓርቲው የስትራቴጂክ ስራ አመራር ዘር ኃላፊ አቶ አንተነህ አየለ የ2019 በጀት ዓመት የየዘርፎች ስትራቴጂያዊ ግቦችና ዋና ዋና ተግባራትን ላይ በሰጡት ማብራሪያ ተግባቦት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል።




