ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን ጎበኙ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በኮንታ ዞን የሚገኘውን የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

​የዚህ ጉብኝት ዋና ዓላማ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመመለስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ሲሆን፣ በሥራ ሂደቱ የሚታዩ ማነቆዎችንና ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ፈጣንና ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሆነ ተገልጿል።

​በጉብኝቱ ወቅት እንደተመላከተው፤ የመደመር መንግስት ዋነኛ እሳቤ ለዘመናት ተከማችተው የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን በደረጃ በመቅረፍ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

​በተለይም ያለፉት ዓመታት የማህበራዊ ልማት ስብራቶችን በመጠገንና በማከም ረገድ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል።

የትውልድ መቅረጫና የበቁ ባለሙያዎች ማፍሪያ የሆኑት የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ያሉ ተቋማት ለስልጠናና ለምርምር ምቹ ከባቢን እንዲፈጥሩ የማድረግ ዓላማን ያነገበ ምልከታ እንደሆነ ተብራርቷል።

​በክልሉ የሚከናወኑ የኮንስትራክሽንና የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴዎችን በውጤታማነት ለመደገፍና የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማፋጠን ቁልፍ ድርሻ እንዳላቸው ተገልጿል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x