በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን እየተሰሩ የሚገኙ የታርጫ-ጪዳ አስፓልት መንገድ፣ የወልድሃኔ ዱርጊ-ዱራሜ መንገድና የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለህዝቡ ጥቅም የሚውሉ መሆን እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
በሚቀጥሉት ወራት በሁሉም ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ በዛብህ በበኩላቸው የሚነሱ ማነቆዎች በተገቢው በመፍታት፤ በሚቀጥሉት 2 እና 3 ወራት በተለይ የታርጫ-ጪዳ መንገድ ካለበት ደረጃ የሚታይ ለውጥ እንዲያስመዘግብ አሳስበዋል።
የወልድሃኔ_ዱርጊ_ዱራሜ መንገድ ግንባታ ዙሪያ ያሉ መነቆዎች የተነሱ ሲሆን በዳውሮ በኩል ያለው ያነሰ አፈፃፀም በፍጥነት እንዲታረም አስገንዝበዋል።
በክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ካሉት ማዕከላት የታርጫው የተሻለ አፈፃፀም ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የመቆራረጥ ጉዳዮች ቢቀረፉ ከተያዘለት ሰኔ 2019 የጊዜ ገደብ ቀድሞ የመጠናቀቅ ዕድል አለው ተብሏል።




