የወልድሃኔ _ዱርጊ_ዱራሜ መንገድ በክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን የተመሩ የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች የወልድሃኔ_ዱርጊ_ዱራሜን የመንገድ ስራ ጎብኝተዋል።

‎ለረጅም ጊዜ የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየው ይህ መንገድ ፤ በመደመር መንግስት ይሁንታ አግኝቶ ወደ ተግባር ተገብቷል።

‎አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 40.11 ኪሎ ሜትር ሲሆን የአፈር ቆረጣ ስራን ጨምር የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል።

‎3 መቶ 40 ሜትር ድልድይ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጥ ጥናት ተደርጎ የጨረታ ሂደት ላይ ይገኛልም ተብሏል።

‎የክልልና የዞን መንግስት በየጊዜው የአፈፃፀም ደረጃውን ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እያበረከተ መሆኑ ተመላክቷል።

‎የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ አስተባባሪ አካላትና ሌሎች አመራሮች በጉብኝቱ ተገኝተዋል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x