ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ የተዘነጉ እንደምዕራብ ኦሞ ዞኖች ያሉትን በመመልከት የመልማት ጥያቄዎችን በአግባቡ የመለሰ ፓርቲ ነው ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በመገኘት ለ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂደዋል።

በዞኑ ጀሙ ከተማ በተካሄደው የይምረጡኝ ቅስቀሳ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ባለፉት ዓመታት በሰጣችሁን ይሁንታ መሰረት ላከናወንነው ተግባራት ከጎናችን መሆናችሁን በይፋ ስለገለጻችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የነበረውን ኋላ ቀርነትና ውስብስብ አሰራር በማስቀረት በብልጽግና እየደመቀች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ባሳየነው ስርዓታዊና ተቋማዊ ለውጥ ህዝባችን ከጎናችን መሆኑን በይፋ አረጋግጧል ብለዋል።

ምንም እንኳ ፓርቲያችን ከውስጥና ከውጭ ተላላኪዎች በርካታ ፈተናዎች የተደቀኑበት የነበር ቢሆንም በጽኑ መሠረት ላይ የተመሠረተ ፓርቲ በመሆኑ ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀልበስ እየተሻገረ ይገኛልም ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ፓርቲያችን ተቀብሮ የቆየውን የባህር በር ጉዳይ ወደ አደባባይ ከማምጣቱም ባሻገር የጉባ ብስራቶች በሚል ይፋ ያደረጋቸው የ30 ቢሊየን ብር ፕሮጀክቶች ትልቅ ማሳያ ናቸው ሲሉ አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል።

ብልጽግና ሰው ተኮር በመሆኑ ከተቸገሩት ጎን ከመሆኑም በላይ ለሴቶችና ወጣቶች በርካታ ስራ ዕድሎችን የፈጠረና እየፈጠረ ያለ ፓርቲ በመሆኑ የለውጥ አራማጅ እና ሀገር የሆነውን ፓርቲ በመምረጥ አጋርነታቸውን እንዲታሳዩ ሲሉ ለምዕራብ ኦሞ ዞን ህዝቦች ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከመስራት ባለፈ ፓርቲው በአብላጫ ድምፅ አሸናፊ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በበኩላቸው ብልጽግና ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ የተዘነጉ እንደምዕራብ ኦሞ ዞኖች ያሉትን በመመልከት የመልማት ጥያቄዎችን በአግባቡ የመለሰ ፓርቲ ነው ብለዋል።

በሀገር መሪ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ዞኑን በመጎብኘት ለልማት ጥያቄ ምላሽ መስጠት የቻሉም የፓርቲው መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በዚህም በዞኑ የመልማት ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ከመሆኑም በላይ አንጻራዊ ሠላምንም ማረጋገጥ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይ የዞኑ ህዝብ የሀገሪቱን ድንበር በማስጠበቅ የራሱን አበርክቶ እየተወጣ ያለ ህዝብ በመሆኑ የክልሉ መንግስት ለዚሁ የሀገራዊነት ግደታ ዕውቅና ይሰጣል ብለዋል።

ይህን ታሳቢ በማድረግ የክልሉ መንግስት ለዞኑ ህዝቦች በርካታ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ብዙ ስራ መሰራቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር በፖለቲካው ዘርፍ የዞኑ ህዝብ በመንግሥት ደረጃ በቂ ውክልና በማግኘት በወንድማማችነትና በጋራ ስሜት ለሀገር ግንባታ በጋራ እንዲሰራ ዕድል ተመቻችቶለታል ብለዋል።

በመሆኑም የዞኑ ህዝብ ከብልጽግና ፓርቲ ጎን በመሆን የታየውን ለውጥ ለማስቀጠልና ያደሩ ጥያቄዎች ዳግም እንዲመለሱ አጋሪነታቸውን በምርጫ ካርድ ልያረጋግጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይ በዞኑ ቤሮና ሱሪ ወረዳዎች የሚስተዋለውን የሠላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት ፓርቲያችን በጀመረው ልክ አጠናክሮ ስራውን ያስቀጥላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ተያይዘንና ተጋግዘን ልማታችንን እንዲናረጋግጥና እንዲናስቀጥል ብልጽግናን መምረጥ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን ለዞኑ ህዝብ አስተላልፈዋል።

May be an image of one or more people, dais and text
May be an image of one or more people and text
0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x