ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ከወጪ ንግድ 2.309 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ በተያዘው የ2019 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሁለት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 309 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግገኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህም የዕቅዱን 103 ነጥብ 82 በመቶ መሳካቱ ተገልጿል።

ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ176 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ የተነገረ ሲሆን፣ በመጠን 310 ሺህ 6 ቶን ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በገቢው የማዕድን ዘርፉ 1 ነጥብ 346 ቢሊዮን ዶላር በማስገኘት ቀዳሚ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በዚሁ ዘርፍ የወርቅ ምርት 1 ነጥብ 344 ቢሊዮን ዶላሩን ይዟል። የግብርናው ዘርፍ ደግሞ 837 ነጥብ 989 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱ ሲነገር፤ ከዚሁ ዘርፍ ቡና 605 ነጥብ 847 ሚሊዮን ዶላር በማስመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ወስዷል።

ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 50 ነጥብ 07 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 74 ነጥብ 912 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት የዕቅዱን 62 ነጥብ 75 በመቶ ማሳካቱንንም ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል። በሌላ በኩል የቆዳና የሥጋ ውጤቶች የተሻለ አፈጻጸም ቢያሳዩም የምግብ፣ መጠጥና የብረታ ብረት ዘርፎች ከዕቅድ በታች ውጤት ማስመዝገባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 0 votes
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x