የመንግስትን አቅጣጫና የህዝቡን እያደገ የመጣ የልማት ፍላጎት መሸከምና ማሻገር የሚያስችል የአመራር መዋቅር የማደራጀት ሥራ ተከናውኗል — ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የሕዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሳካትና የክልሉን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ የሚያስችል የአመራር ምደባና የመንግስት ምስረታ ሥራ ማከናወኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን መንግስት ምስረታና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክተው ለሚዲያ አካላት በሰጡት የፕሬስ ኮንፈረንስ መግለጫ፣ የመደመር መንግስት ኢትዮጵያን የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የክልሉ መንግስትም…

