የፌዴራሊዝም ስርዓት ክልሎች ያላቸውን ሀብት በነፃነት እንዲጠቀሙ የሚያስችል በመሆኑ የክልላችንን ማዕድንና ሌሎች ሀብቶች በተገቢው መንገድ መምራት እና ማስተዳደር ይገባል – ርዕሰመስተዳድር ፍቅሬ አማን
የማዕድን ሀብት ክልሉ ካለው የተፈጥሮ ሀብት ዋነኛው እና በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ዕድገት ላይ የድርሻውን እየተወጣ ያለ ዘርፍ በመሆኑ ዘርፉን ማዘመንና በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባ ርዕሰመስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉን መንግስት ምስረታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚዲያ አካላት በሰጡት የፕሬስ ኮንፈረስ መግለጫ ክልሉ ያለውን እምቅ ጸጋ በአግባቡ መጠቀም እንዲችል የሚያደርግ የአመራር ምደባ መደረጉን ተናግረዋል።…

